ማለዳ ፎም ከ አርቲስት እና ሞዴል ሩታ መንግስተአብ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ፈፀመ።

ማለዳ ፎም ከ አርቲስት እና ሞዴል ሩታ መንግስተአብ ጋር የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት መፈፀሙን ሲገልፅ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል።

ማለዳ ፎም የሃገራችንን የፎም ኢንደስትሪ በተቀላቀለ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከመሪዎቹ ተርታ መሰለፍ የቻለ ሰፊ የገበያ ድርሻ እና ተቀባይነትን ማትረፍ የቻለ ዘመናዊ ተቋም ሲሆን በዘርፉ የመጨረሻውን ፎሚንግ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የጥራት ደረጃቸው እጅግ ከፍተኛ የሆኑ የፎም እና ቦንድድ ምርቶችን በማቅረብ የላቀ አመኔታን ከደንበኞቹ ዘንድ ማትረፍ ችሏል።

ማለዳ ፎም ከፍተኛ ምቾት እና ጥራት ያላቸውን እና ለሰላማዊ ምሽቶች ዋስትና የሆኑ ዘመናዊ ፍራሾችን እያመረተ ለሃገር ውስጥ ገበያ በሰፊው እያቀረበ ሲሆን የድርጅቱ ዋነኛ እሴቶች በሆነው ማህበራዊ ሃላፊነቶችን በመወጣት ረገድም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ተቋም ነው።

ከአርቲስት እና ሞዴል ሩታ መንግስተአብ ጋር ይህንን የብራንድ አምባሳደርነት ስምምነት ስናደርግ ድርጅታችን የመልካም ስብዕና እና የጠንካራ ስራ ውጤት እንደመሆኑ መጠን የእነዚህ ስብእናዎች ባለቤት የሆነችው አርቲስት ሩታ መንግስተአብ ድርጅታችንን በተገቢው መንገድ መወከል እንደምትችል እርግጠኞች በመሆን ምርጫችን ሆናለች::